የአዘርባጃን አውሮፕላን አደጋ የተከሰከሰው “በውጫዊ ጣልቃ ገብነት ነው” ተባለ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዘርባጃን አየር መንገድ በካዛኪስታን የተከሰተው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ መንስዔ “ከውጭ የተፈጸመ አካላዊ እና ቴክኒካዊ ጣልቃ ገብነት ነው” ብሏል፡፡
አውሮፕላኑ ከውጭ የመጣ ጣልቃ ገብነት ከገጠመው በኋላ መከስከሱን አየር መንገዱ ገልጿል ሲል ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
አዘርባጃን ብሔራዊ የሐዘን ቀን ያወጀችበት እና የ38 ሰዎች ሕይወት የተቀጠፈበት የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ መንስዔ ምርመራ አለመጠናቀቁም ነው የተገለጸው፡፡
62 መንገደኞችንና አምስት ሠራተኞችን ያሳፈረ የአዘርባጃን አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በካዛኪስታን አክታው ከተማ አቅራቢያ ባሳለፍነው ረቡዕ መከስከሱ ይታወሳል፡፡