አቶ አደም ፋራህ የከተራ እና የጥምቀት በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የከተራ እና የጥምቀት በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አቶ አደም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት” ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ” ብለዋል።
በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡