Fana: At a Speed of Life!

የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በከፍተኛ መነሳሳት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና የህዝብን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በከፍተኛ መነሳሳት መሥራት እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የ2ኛውን የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ክልላዊ ቅድመ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚህ ወቅት ÷በቅድመ ጉባኤ በተደረገው ውይይት በሀገራዊና ክልላዊ አጃንዳዎች ላይ በጥልቀት ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

ኮንፈረንሱ የጋራ መግባባት ላይ ከመድረስ ባለፈ የአመራርና የአባላት የሀሳብና የአመለካከት አንድነት በመፍጠር ለቀጣይ ድርጅታዊና መንግሥታዊ ተልዕኮዎች ዝግጁ ማድረግ የተቻለበት መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

“በክልሉ ሰላምን የበለጠ ለማፅናትና አስተማማኝ ህዝባዊ መሠረት እንዲይዝ ለማድረግ ፣ በየዘርፉ ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና የህዝብን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በከፍተኛ መነሳሳት መሥራት ይገባል” ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.