Fana: At a Speed of Life!

ከ469 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ዘመናዊ የፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ግንባታ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ከ469 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀጂራ ኢብራሂም÷ የአሶሳ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የከተማዋን የፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ ለማጣራትም ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በተደረገው ስምምነት ከሁለት ወራት በፊት ከ469 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የፍሳሽ ማጠሪያ ግንባታ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀው ግንባታው ንጽህ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ ተረፈ ምርቱም ለተለያዩ የግብርና ስራዎች እንደሚውል መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.