ዎከር ወደ ኤሲሚላን …
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የማንቼስተር ሲቲ የክንፍ ተከላካይ ካይል ዎከር በውሰት ውል ወደ ጣሊያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን ለመዘዋወር ከስምምነት መድረሱ ተሰምቷል፡፡
በውሉ መሰረት ኤሲሚላን የ34 ዓመቱን ተጫዋች በቋሚነት የማስፈርም መብት ማግኘቱ ተነግሯል፡፡
የውኃ ሰማያዊዮቹ አምበል ዝውውሩን ለማጠናቀቅ እና የሕክምና ምርመራውን ለማድረግ ነገ ወደ ጣሊያን ያቀናል፡፡