Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ለምርታማነት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 22ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የክልሉ መንግስት የ2017በጀት ዓመት እቅድ ክንውን አፈጻጸም ላይ በስፋት እንደሚመክር ተመላክቷል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በቀረቡለት ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በዚህ ወቅት÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከድህነት ለመውጣት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በቱሪዝምና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው ብለዋል ፡፡

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን በመፈተሽ እየተሰራ ስለመሆኑ መግለጻቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.