Fana: At a Speed of Life!

በአማራና አፋር ክልል የተቀናጀ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራና አፋር ክልል የተቀናጀ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በአማራ ክልል የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራው በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረቱ ተናግረዋል፡፡

አቶ እስመለዓለም ምህረቱ ለፋናሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት በክልሉ ከ 366 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተቀናጀ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ የሚከናወንበት ሲሆን ከ 9 ሺህ በላይ ተፋሰሶች የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ እንደሚሰራባቸው ተናግረዋል።

በክልሉ የተቀናጀ ንቅናቄው እስከ 30 ተከታታይ ቀናት ሊቆይ እንደሚችልም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የተቀናጀ ተፋሰስ እና ግጦሽ መሬት ልማት ክልላዊ የማህበረሰብ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአፋር ክልል በጭፍራ ወረዳ ተጀምሯል ፡፡

ንቅናቄው “የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ እንደሚገኝ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በዙፋን ካሳሁን።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.