አየር ወለድ ለሀገር ሉዓላዊነት መስዋዕት የከፈሉ የሀገር ባለውለታዎች ናቸው-ሌ/ጄ ሹማ አብደታ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአየር ወለድ ሠራዊት ለሀገር ሉዓላዊነትና ለህዝብ ክብር ከፍተኛ መስዋዕት የከፈሉ የሀገር ባለውለታዎች ናቸው ሲሉ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገለጹ፡፡
ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በቢሾፍቱ አየር ወለድ ትምህርት ቤት የአየር ወለድ ሥልጠናን አሥጀምረዋል።
ዋና አዛዡ በዚህ ወቅት ÷አየር ወለድ ማለት ወደር በሌለው ጀግንነት ለላቀ ግዳጅና ድል መዘጋጀት ማለት መሆኑን በመግለፅ፤ ሰልጣኞች ከዚህ አኳያ መዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሠራዊት ታሪክ ውስጥ የአየር ወለድ ሠራዊት ለሀገር ሉዓላዊነትና ለህዝብ ክብር ከፍተኛ መስዋዕት የከፈሉ የሀገር ባለውለታ ናቸው ሲሉም መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡