Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢቲሃድ ስታዲየም ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 2፡30 ላይ በሚደረገው ጨዋታ ሩበን ዲያዝ እና ጀረሚ ዶኩ በጉዳት የማይሰለፉ ሲሆን÷አዲስ ፈራሚዎቹ ኦማር ማርሙሽ፣ ቪቶር ሬይስ እና አብዱኮዲረ ኩሳኖቭ በማንቼስተር ሲቲ የቡድን ስብስብ ውስጥ እንደሚኖሩ አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ አስታውቀዋል፡፡

በቼልሲ በኩል ሌቪ ኮልዊል እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ ከጉዳት መልስ ለጨዋታው ብቁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ቦርንማውዝ ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ብራይተን ከኤቨርትን፣ ሊቨርፑል ከኢፕስዊች ታውን፣ ሳውዝሃምፕተን ከኒውካስል ዩናይትድ እንዲሁም ዎልቭስ ከአርሰናል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ሊቨርፑል በ50 ነጥብ ሲመራ÷አርሰናል እና ኖቲንግሃም ፎረሰት በእኩል 44 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.