Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ማርታ የ3000 ሜትር ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በካዛኪስታን ዋና ከተማ አስታን በተካሄደ ከ18 ዓመት በታች የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፋለች።

 

የ16 ዓመቷ አትሌት ማርታ ርቀቱን ለመጨረስ 8 ደቂቃ ከ39 ሰኮንድ ከ80 ማይክሮ ሰኮንድ የሆነ ጊዜ የወሰደባት ሲሆን ከዚህ በፊት ፈጣኑ ሰዓት 8 ደቂቃ ከ40 ሰኮንድ እንደነበር የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመለክታል።

 

እሷን ተከትለው ኢትዮጵያውያን አትሌቶቹ ጉሚ ሽቶ እና አምባዬ አክሱማዊት ውድድሩን ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.