ማንቸስተር ሲቲ ቼልሲን 3 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ማንቸስተር ሲቲ ቼልሲን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ምሽት 2፡30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ቼልሲ በኖኒ ማዱኬ ጎል ሲመራ ቢቆይም ባለሜዳው ማንቸስተር ሲቲ በኧርሊንግ ሃላንድ፣ በተከላካዩ ዮሽኮ ግቫርዲዮል እና በፊል ፎደን ጎሎች ማሸነፍ ችሏል።
ማንቸስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከኒውካስል እኩል 41 ነጥብ ይዞ በግብ ክፍያ 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
ሊቨርፑል ሊጉን አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ53 ነጥብ ሲመራ አርሰናል በ47 ሁለተኛ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት በ 44 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።