አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ የኦሳካ ማራቶን ውድድርን አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ በጃፓን ኦሳካ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆነች።
አትሌቷ ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ የፈጀባት ሲሆን ባለፈው ዓመት በቦታው ውድድሩን ስታሸነፍ ካስመዘገበችው 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ51 ሰኮንድ ጋር ሲነጻጸር በ2 ደቂቃ ከ51 ሰኮንዶች ዘግይታለች።
አትሌት ወርቅነሽ ከውድድሩ በኋላ በሰጠችው አስተያየት፤ የአምናውን ድሌን በማስጠበቄ ደስተኛ ነኝ፣ የወደፊት ግቤ ብቃቴን የበለጠ ማሻሻል ነው ብላለች።
በውድድሩ ጃፓናውያኑ አትሌቶች ካና ኮባያሺ እና ዩካ ሱዙኪ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ማጠናቀቃቸውን ወርልድ አትሌቲክስ ዘግቧል።
የኦሳካ ማራቶን በወርልድ አትሌቲክስ የፕላቲኒዬም ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር መሆኑ ተመላክቷል።
በቴዎድሮስ ሳህለ