የፌደራል ፖሊስ ስዋት በዓለም አቀፉ ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር ለመሳተፍ ልምምድ እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2025 ዓለም አቀፍ የፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር ለመሳተፍ ወደ ዱባይ ያቀናው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን (ስዋት) ልምምድ እያደረገ ነው፡፡
ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድኑ አልሩዋይ ከተማ በሚገኘው የስዋት ቻሌንጅ ማሰልጠኛ ማዕከል ነው ልምምድ እያደረገ የሚገኘው፡፡
በፈረንጆቹ 2025 የፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር ቡድኑ ኢትዮጵያን በመወከል በታክቲካል ኦፕሬሽን ቻሌንጅ፣ በጥቃት፣ በቪአይፒ አመራር የማዳን ተልዕኮ፣ በከፍተኛ ማማ መውጣትና መውረድ እንዲሁም በመሰናክል ኮርስ ይወዳደራል ተብሏል፡፡