ጉምሩክ ኮሚሽን ከ203 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ 203 ነጥብ 75 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ በስድስት ወራት 190 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ መሰራቱን ተናግረዋል።
በዚህም 203 ነጥብ 75 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ጠቅሰው፤ የእቅዱን 106 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።
ገቢው የተሰበሰበው ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከሌሎች ታክስ እና ታክስ ካልሆኑ አርዕስቶች መሆኑን መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ቁጥጥር በተሰሩ ስራዎች 107 ቢሊየን 243 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉንም አንስተዋል።