ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐግብር ከቀኑ 9 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚደረገው በዚህ ጨዋታ 28 ነጥቦችን በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ የተቀመጡት ፈረሰኞቹ 22 ነጥቦችን በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ቡናማዎቹ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በሌላ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት 13 ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ሲዳማ ቡና በሊጉ ወራጅ ቀጣና ላይ ከሚገኘው ስሑል ሽረ ጋር ይፋለማል፡፡