Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 1፡30 አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በሊጉ ጨዋታዎች 47 ነጥቦችን በመሰብሰብ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አርሰናል ከመሪው ሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ይፋለማል፡፡

በተመሳሳይ ከአርሰናል በስድስት ነጥብ ልዩነት 41 ነጥቦችን በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ 4ኛ ላይ የተቀመጠው ማንቼስተር ሲቲ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርግም ይጠበቃል፡፡

በሌላ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ቀን 11:00 ብሬንትፎርድ ከ ቶተንሀም በተመሳሳይ ሰዓት ማንቸስተር ዩናይትድ ከክሪስቲያል ፓላስ ጋር በኦልድትራፎርድ ስታድየም ይጫወታሉ፡፡

ሊጉን ሊቨርፑል በ56 ነጥብ እየመራ ሲሆን አርሰናል እና ኖቲንግሀም ፎረስት 47 ነጥብ በመያዝ በእኩል ነጥብና በጎል ልዩነት እየተከተሉ ይገኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.