Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ÷የፌዴራል የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እያቀረቡ ነው፡፡

ባቀረቡት ሪፖርት÷ከዚህ በፊት ኢንስቲትዩቱ በፍትህ ሚኒስቴር ስር በነበረበት ወቅት የዳኝነት አካሉን ፍላጎት በአግባቡ አሟልቶ ስራን በአግባቡ ከመስራት አንጻር ክፍተት የሚታይበት እንደነበር ገልፀውዋል፡፡

በዚህም የዳኝነት አካሉ ነጻነትና ገለልተኝነትን የበለጠ ለመጠበቅ ሲባል ኢንስቲትዩቱን ማቋቋም ማስፈለጉንና ለዚህም ረቅቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በዳኝነትና በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ለውጥ ማምጣት የሚችል በእውቀት፣ በክህሎት፣ በአመለካከትና በስነ ምግባሩ ብቁ የሆነ የዳኝነትና የፍትህ አካል ባለሙያ እና አመራር ለማፍራት በተጨማሪም ጠንካራ ኢንስቲትዩት ማቋቋም በማስፈለጉም ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱ የ17ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤንም በሙሉ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን÷ሶስት ረቂቅ አዋጆችን አስመልክቶ የሚቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብም መርምሮ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.