Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ በባሕር ዳር ከተማ እየተወያዩ ነው።

ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ፥ ውይይቱ የጉባኤውን ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ወደ ሁሉም መሪዎች እና ወደ ሕዝቡ በማውረድ ለሀገር እድገት በሚበጅ መልኩ በተግባር ለመተርጎም ያለመ ነው ብለዋል።

የክልሉ ወቅታዊ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ተነስተው ምክክር እንደሚካሄድ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡም አመላክተዋል።

የተቋማትን የሥራ አፈጻጸም ደረጃ በመፈተሽ የበለጠ በጠነከረ መልኩ ለሕዝብና ለሀገር እንዲሠሩ የሚያስችል ምክክርም ይካሄዳል ነው ያሉት።

በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ፥ ፓርቲው በ2ኛ መደበኛ ጉባኤው ሊከናወኑ በሚገባቸው አንኳር ተግባራት ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የተለያዩ ውሳኔዎችን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

ውሳኔዎች ሀገርና ሕዝብን በሚጠቅም መልኩ እንዲተገበሩ ጥልቅ ግንዛቤ እና የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊው፣ በጉባኤው የተላለፉ አቅጣጫዎችን በመከተል ለሀገር እድገት እና ሰላም መሥራት ተገቢ መሆኑን መናገራቸውን የዘገበው አሚኮ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.