ከአንዲት እናት 11 ነጥብ 2 ኪሎ የሚመዝን ዕጢ በቀዶ ሕክምና ተወገደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሲ ዞን በቆጂ ሆስፒታል ከአንዲት እናት 11 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጢ በቀዶ ሕክምና መወገዱ ተገልጿል፡፡
የ45 አመቷ እናት ዕጢው ለአምስት አመታት አብሯቸው እንደቆየም ተነግሯል፡፡
ዕጢው በተሳካ ቀዶ ሕክምና ከተወገደላቸው በኋላ ጤንነታቸው በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክትር ዶክተር ኃይላይ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
በአብደላ አማን