Fana: At a Speed of Life!

ሃማስ ተጨማሪ ሶስት እስራኤላዊያን ታጋቾችን ለቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ ታግተው የቆዩ ተጨማሪ ሶስት የእስራኤል ዜጎችን መልቀቁን አስታወቀ፡፡

ታጋቾቹ ወደ ቀይ መስቀል ከመተላለፋቸው በፊት በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው እና ዴይር አል ባላህ በተሰኘው አካባቢ ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ይፋ መደረጋቸው ተገልጿል፡፡

ኢል ሻራቢ፣ኦሃድ ቤን አሚ እና ኦር ሌቪ የተባሉት ታጋቾች በቀይ መስቀል አማካኝነት ለእስራኤል ጦር የሚሰጡ ሲሆን÷ ከሰዓታት በኋላ ቤተሰቦቻቸውን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተጋቾቹ ሃማስ በድንገት በፈጸመው ጥቃት ከደቡባዊ እስራኤል ተወስደው በሃማስ ቁጥጥር ስር የነበሩ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ታጋቾቹ ከበፊቱ የፊት ገጽታቸው በተለየ መልኩ ተጎሳቁለው እና ደክመው መታየታቸውም እስራኤልን አስቆጥቷል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ሃማስ ተጋቾቹን ሲያሰቃይ እንደነበር ጠቅሰው፤ይህም በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ነው ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡

በምላሹ እስራኤል 183 የጦር እስረኞችን እንደምትለቅ መገለጹንም ቢቢሲ እና ዲ ደብሊው በዘገባቸው ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.