Fana: At a Speed of Life!

13ኛው የሀዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 13ኛው የሀዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ፡፡

21ኪሎ ሜትር በሸፈነው በዚህ ውድድር በወንዶች አትሌት አስቻለው ብሩ ፣በሴቶች ደግሞ ምህረት ገመዳ አሸንፈዋል።

በውድድሩ ከአዋቂዎች ውድድር በተጨማሪ የ 8 ኪ.ሜ የጤና ሯጮች እና የህፃናት ውድድር ተደርጓል።

ውድድሩ በአራት ከተሞች ማለትም በሀዋሳ፥ጅማ፥አርባ ምንጭ እና በቆጂ “ልወቅሽ ኢትዮጵያ ” በሚል እንደሚካሄድም ታውቋል።

በኢትዮጵያ ብቸኛ የሐይቅ ዳር ሩጫ ውድድር የሆነው የሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን ለከተማዋ መልካም ገፅታ የሚፈጥርላት መሆኑ ተነግሯል።

በዳዊት መሐሪ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.