Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲያገኙ የታየው ቁርጠኝነት ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት መሪዎች የአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲያገኙ ያሳዩት ቁርጠኝነትና አጋርነት ለሌሎች ምሳሌ እንደሚሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ እና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የጋራ የመሪዎች ስብሰባ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ተካሄዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ÷ኢትዮጵያ በስብሰባው የተገኙ ውጤቶች እና ውሳኔዎችን በመልካም ጎኑ እንደምታያቸው ገልጿል።

ኢትዮጵያ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን (ዶ/ር)፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ሊቀመንበር ዊሊያም ሩቶ (ዶ/ር) እና የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት እና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ሊቀመንበር ኤመርሰን ምናንጋግዋ ስብሰባው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያሳዩትን አመራር አድንቃለች።

ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የማበጀት መንፈስ ቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ያሳዩት ትብብር እና ቁርጠኝነት ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ተግባር ነው ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.