በእንጅባራ ከአንዲት እናት 24 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጢ በቀዶ ሕክምና ተወገደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ከአንዲት እናት 24 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጢ በቀዶ ሕክምና መወገዱ ተገልጿል፡፡
የ38 ዓመት ታካሚዋ ወ/ሮ ትሁን ገነቱ በፓዌ ልዩ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ÷ሁለት ሰዓት አካባቢ የወሰደ የተሳካ ከባድ ቀዶ ሕክምና አድርገው ለ2 ዓመታት አብሯቸው የቆየው አላስፈላጊ ዕጢ ተወግዶላቸዋል ተብሏል፡፡
ቀዶ ጥገናው በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ቡድኑ በማህፀንና የወሊድ ስፔሻሊስት ዶ/ር ማርቆስ አዲሱ የተመራ እንደነበርም የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ሀይሉ ተናግረዋል።
ታካሚዋ በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ መገለጹንም የአዊ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡