የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና የ46ኛው የሥራ አስፈፃሚዎች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ ተሳታፊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሌሎች እንግዶች አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡
በዚህ መሰረትም የጋምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማማዶ ታንጋራ (ዶ/ር) እና የሴኔጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያሲን ፎል እና አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡