Fana: At a Speed of Life!

በጥሎ ማለፉ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲደርጉ ማንቼስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

በጥሎ ማለፉ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ቀደም ብሎ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ የፈረንሳይ ቡድኖች የሆኑት ብረስት እና ፒኤስጂ ይፋለማሉ፡፡

የማንቼስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በኤቲሃድ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ሁለቱ ቡድኖች በመድረኩ 12 ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡

በሁለቱ ቡድኖች የእርስ በርስ ግንኙነት ሪያል ማድሪድ 4 ጊዜ ድል ሲቀናው ማንቼስተር ሲቲ 3 ጊዜ በማሸነፍ 5 ጊዜ ደግሞ አቻ መለያየት ችለዋል፡፡

የተከላካይ መስመር ተጨዋቾቹን በጉዳት ያጣው የአውሮፓው ሃያል ሪያል ማድሪድ በኪሊያን ምባፔ በሚመራው የፊት መስመር ተማምኗል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በውድድር ዘመኑ ደከማ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን በርካታ ግዢዎችን በጥር የዝውውር መስኮት በመፈጸም ቡድኑን ለመገንባት ቢሞክርም የቀደመው አስፈሪው ግርማ ሞገሱ አብሮት አይገኝም፡፡

ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የኢንግሊዝ ክለቦችን 13 ጊዜ ከውድድሩ በማሰናበት ታሪካዊ የበላይነት አለው፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት በሚደርጉ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ መረሃ ግብሮች ጁቬንቱስ ከፒኤስቪ እንዲሁም ስፖርቲንግ ሊዝበን ከቦሩሺያ ዶርቱመንድ ይጫወታሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.