Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 1 ሺህ 40 ፕሮጀክቶች በበጀት ዓመቱ ይጠናቀቃሉ ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት በአማራ ክልል 1 ሺህ 40 ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ እየተካሄደ በሚገኘው የአማራ ክልል ም/ቤት መደበኛ ጉባዔ ላይ ÷የክልሉን የ6 ወራት የልማትና የመልካም አሥተዳደር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርታቸውም ለክልሉ ከጸደቀው 150 ነጥብ 6 ቢሊየን በጀት ውስጥ ባለፉት ስድስት ወራት 34 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 30 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ሥራዎች ማስፈጸሚያ ቀሪው 3 ነጥብ 59 ቢሊየን ብር ደግሞ ለካፒታል ሥራዎች ወጪ ተደርጓል ብለዋል።

ያለውን ውስን ሃብት በመጠቀም የተጀመሩ የካፒታል ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በዚህ ዓመት ለመመረቅ እና ወደ ልማት ለማስገባት ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም አስረድተዋል፡፡

ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል 17 ነጥብ 43 ቢሊየን ብር መመደቡን ገልፀው ÷1 ሺህ 40 የሚሆኑት ፕሮጀክቶች በ2017 በጀት ዓመት እንደሚጠናቀቁ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.