ኮሚሽኑ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ስኬታማነት የኃይማኖት ተቋማት ትብብርን ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017(ኤፍ ኤም) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ከሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በምክክሩ ሂደትና ተሳትፎ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸው መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ÷ ኮሚሽኑ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰራው ስራና ላስመዘገበው ውጤት የኃይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ እንደነበር አውስተዋል፡፡
ኮሚሽኑ ስኬታማ ውጤቶችን እንዲያስመዘግብ የኃይማኖት ተቋማት ላበረከቱት አስተዋፅዖም ዋና ኮሚሽሩ ምስጋና ማቅረባቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በቀጣይ የሚደረገው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን የኃይማኖት ተቋማት የተለመደውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።