ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከናይጀሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሱፍ ማይታማ ተገር ጋር በሁለትዮሽ እና አሕጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮች ላይ መክረዋል።
በተመሳሳይ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሀመድ ኦማር ጋር ባደረጉት ውይይት በሁለትዮሽ እና በአካባቢያዊ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡