የሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ሁለተኛ ቀን የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡
በዚህ መሰረት ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ የቤልጂዬሙ ክለብ ብሩጅ ከጣልያኑ አታላንታ ጋር ይፋለማሉ፡፡
ምሽት 5 ሰዓት ላይ የስኮትላንዱ ሴልቲክ በሴልቲክ ፓርክ ስታዲየም ከባየርንሙኒክ፣ የሆላንዱ ፌይኑርድ ከኤሲሚላን እንዲሁም ሞናኮ በስታዴ ሉዊስ ሁለተኛ ስታዲየም ከቤኔፊካ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ትላንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ተጠባቂ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ ባለሜዳውን ማንቼስተር ሲቲ 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔ፣ ብራሂም ዲያዝ እና ጁድ ቤሊንግሃም ባስቆጠሯቸው ግቦች ሁለት ጊዜ ከመመራት ተነስቶ ማንቼስተር ሲቲን ማሸነፍ ሲችል ኤርሊንግ ሃላንድ ሁለቱን የሲቲ ግቦች አስቆጥሯል፡፡
በሌሎች የምሽቱ መርሐ ግብሮች ፒ ኤስ ጂ ብረስትን 3 ለ 0፣ ጁቬንቱስ ፒኤስቪን 2 ለ 1 እንዲሁም ቦሩሺያ ዶርቱሙንድ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡