Fana: At a Speed of Life!

የታላቁ ረመዳን ወር አቀባበልን አስመልክቶ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የታላቁ ረመዳን ወር አቀባበልን አስመልክቶ የኡለማዎች፣የኢማሞችና የዱአቶች ኮንፈረስ እያካሄደ ነው ።

በኮንፈረሱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ እና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ እና ኡለማዎች ፣ኢማዎች እንዲሁም ዳኢዎች ተገኝተዋል።

ኮንፈረንሱ በዋናነት ሰላምን ከማስጠበቅ አኳያ የኡለማዎች ሀላፊነት ምን መሆን አለበት?ታላቁ የረመዳን ወርን እንዴት እንቀበል? በሚሉና የሀሳብ ግጭቶች አፈታት በኢስላም በሚሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ በዚህ ወቅት÷እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ በበኩላቸው÷”ታላቁ የረመዳን ወርን ስንቀበል የእስልምና ሀይማኖት አስተምህሮዎችን የምንተገብርበት መሆን አለበት “ብለዋል፡፡

1446 አመተ ሂጅራ የረመዳን ወርን ተውበት በማድረግ ወደአላህ በመመለስ በተለያየ ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በማቋቋም መሆን እንዳለበት እንዲሁም ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን አረጋዊያን መደገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.