የአፋር ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1ኛ .አቶ ኡመር ኑር አርባ- የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ
2ኛ. አቶ ሀሚድ ዱላ -በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የማህበራዊ ክላስተር
አስተባባሪና የክልሉ ስፖርት ፣ወጣቶችና ባህል ቢሮ ሃላፊ
3ኛ አቶ አሊ መሀመድ ማህሙድ -በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ
4ኛ.አቶ አህመድ ሁሴን- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ልማት ድርጅቶች ሃላፊ
5ኛ.አቶ መሀመድ ሁሴን- የብልፅግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ
6ኛ. አቶ ሙሳ አደም- የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ
7ኛ.አቶ አህመድ ኢብራሂም -የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ
8ኛ ወይዘሮ አሚና ሴኮ -የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ
እንዲሁም አቶ ሀሰን መሀመድ ሀሰን -የክልሉ ዋና ኦዲተር ምክትል ሃላፊ ሆነው እንዲሾሙ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የቀረበውን ሹመት ምክር ቤቱ መርምሮ አጽድቋል፡፡
ተሻሚዎቹም የተጣለባቸዉን ህዝባዊ ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ቃለመሃላ ፈጽመዋል፡፡
በሌላ በኩል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ የነበሩት አቶ ኢሴ አደም ደግሞ ያለመከሰስ መብታቸው መነሳቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡