የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሌ በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎቸ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል፡፡
በመላኩ ገድፍ እና ብሩክታዊት አፈሩ