የሴኔጋል ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የፍትህ ሚኒስትሯ ሀና አርአያ ስላሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ ከፊታችን የካቲት 8 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ይታወቃል።
በፌቨን ቢሻው እና ብሩክታዊት አፈሩ