የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ዩማ ቡይካይ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ ኢድሪስ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ ከፊታችን የካቲት 8 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ይታወቃል።
በፌቨን ቢሻው እና ብሩክታዊት አፈሩ