Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት የዳኞችን ሹመት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ለአራተኛ ቀን ቀጥሏል።

ምክር ቤቱ በአራተኛ ቀን የጉባኤ ውሎው የክልሉን ፍርድ ቤቶች ማጠናከሪያ ረቂቅ አዋጅ፣ የባሕል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና ዕውቅና ለመስጠት የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣ ፍትሕ እና የሕግ ኢንስቲትዩት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ እና የፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ደንብን መርምሮ አጽድቋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የክልሉ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡

እነዚህም 9 ዳኞች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ሦስት ዳኞች ለከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንት፣ 46 ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች እና 171 ዳኞች ለወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ናቸው።

ምክር ቤቱ ከባድ የሥነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ ሁለት ዳኞችን ለሦስት ዓመታት ከሥራ ማገዱን አሚኮ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.