ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ እንኳን በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መጡ ብለዋል።
በተደጋጋሚ የምናደርጋቸው ግንኙነቶች ቁርኝቶቻችንን በማጠናከር ትብብራችንን ይበልጥ ለማጎልበት ቁልፍ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።