አፍሪካ በጠንካራ አመራር እስከተመራች ድረስ ሰፋፊ እድሎች አሏት – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሴኔጋል ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ጋር መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት መረጃ ገልጸዋል።
በሚገጥሙን ፈተናዎች ውስጥም ሆነን በጠንካራ አመራር እስከተመራች አህጉራችን አፍሪካ ሰፋፊ እድሎች ያሏት መሆኗን አውስተናል ብለዋል።
ለሁለቱም ሀገራት የጋራ ጥቅም እንዲሁም ለአፍሪካ ፋይዳ ሲባል እነዚህን እድሎች በጋራ ለመጠቀም አብሮ ለመሥራት መስማማታቸውንም ጠቁመዋል።