የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማምሻውን የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት መሐመድ ቢ.ኤስ ጃሎ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተመሳሳይ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ማምሻውን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪዊያንና ዘርዓ-አፍሪካዊያን” በሚል መሪ ሃሳብ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል፡፡