Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጤና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 231 የሕክምና ዶክተሮችን ጨምሮ 366 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ በሕክምናና ፋርማሲ ዘርፍ ካስመረቃቸው 366 ተማሪዎች ውስጥ 112 ያህሉ ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በሕክምና ለ40ኛ ጊዜ በፋርማሲ ደግሞ ለ21 ጊዜ ነው ተማሪዎችን ያስመረቀው፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ  የጤና ሚኒስትር  ዴዔታ ዶክተር  ደረጄ ዱጉማ፣ የዩኒቨርሲቲው  ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) እና የዞንና የጎንደር  ከተማ አስተዳደር  አመራሮች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው  በህክምናው ዘርፍ አንቱታን ያተረፈ   ዩኒቨርሲቲ ነው ብለዋል።

ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በበኩላቸው÷ተመራቂዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመት እና የሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓልም ከጥር 13 ቀን ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

በተስፋዬ አባተ እና ጳውሎስ አየለ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.