የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራማ ፎሳ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራማ ፎሳ በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕልን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የመሪዎች ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ እና ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡