Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ ለዳይሬክተሯ በአረንጓዴ አሻራ፣ የኮሪደር ልማት፣ እየተሰሩ ባሉ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች እና የኤሌክትሮኒክስ አስተዳድር ኢንሼቲቮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸውም ኢትዮጵያ ከዩኤንዲፒ ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትን ያደነቁት አሁና ኢዚያኮንዋ በበኩላቸው÷ ተቋማቸው ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.