ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት 38ኛው የመሪዎች ጉባዔ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ካስተላለፉት መልዕክት:-
👉 የመደመር ፍልስፍና ብዝኃነትን እና ህብረትን ለማጠናከር ቁልፍ ሚና እንዳለው ሁሉ ፓን አፍሪካኒዝምንም ለማጠናከር ያግዛል፣
👉 በቅኝ ግዛት የመጣብንን ጠባሳ ራስን በመቻል እና ድህነትን በማሸነፍ ማሻር ይገባናል፤ ለዚህም የተለያዩ ዘመናዊ የግብርና ትልሞችን ተግባራዊ በማድረግ፣ በምግብ ራስን መቻል እና ድህነትን ማሸነፍ አለብን፣
👉 ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የተለያዩ ዘመኑን የዋጁ የግብርና ትልሞችን በመጠቀም ከአፍሪካ አንደኛ ስንዴ አምራች ሀገር መሆን ችላለች፣
👉 ለቀጣዩ ትውልድ ዘመን ተሻጋሪ መሰረት ለመጣል አፍሪካዊ ዳያስፓራውን ማነቃቃት እና ማሳተፍ ያስፈልጋል፣
👉 በአፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ በጋራ በመደመር አፍሪካውያን የምንፈልጋትን የበለጸገች አህጉር መፍጠር እንችላለን፤ የቅኝ ግዛት ጠባሳችን በዚህ ነው የሚድነው፣
👉 የአፍሪካ የካሳ ጥያቄ ከቃል ባለፈ ፍትህ የማስፈን ጥያቄ ነው፤ ማንኛውም የሰው ዘር በእኩልነት ተከብሮ ይኖር ዘንድ ፍትህ ማስፈን ወሳኝ ነው፣
👉 በአፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ በቅኝ ገዢዎች በጂኦ ፖለቲካዊና መሰል መጥፎ አሻራዎች ፍትህ ሊያገኙ ይገባል፣
👉 የአህጉራችን የተሟላ ዕምቅ አቅም ለመጠቀም መላው አባል ሀገራት ትብብርና አጋርነት በማጠናከር መስራት አለብን፣
👉 በፍጥነት እያደገ ባለው ዲጂታል ምህዳር ላይ ተወዳዳሪ ተጫዋቾች መሆናችንን ለማረጋገጥ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ላይ በንቃት መሳተፍ አለባት፣
👉 በፍጥነት እያደገ የመጣው ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢኮኖሚያችንንና ማህበረሰባችንን ለማሸጋገር ከፍተኛ አቅም አለው፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ታዳሽ ኃይል እና ሞባይል ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመተባበር እንደ አየር ንብረት ለውጥ፣ የመሰረተ ለማት ክፍተትና የህብረተሰብ ጤና ችግር የመሳሰሉ የጋራ ተግዳሮቶቻችንን ለመፍታት ያስችላል፣
👉 በዘመኑ የቴክኖሎጂና ትምህርት በማጠናከር አፍሪካ በዓለም የቴክኖሎጂ ስልጣኔዎች ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን ለዓለም ስልጣኔም ወሳኝ አበርክቶ የሚኖራት አህጉር ትሆን ዘንድ በጋራ መስራት ይገባል።