Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እስክታገኝ ድረስ ጥረት ማድረግ እንደሚቀጥሉ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እስክታገኝ ድረስ ጥረት ማድረግ እንደሚቀጥሉ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ።

እየተካሄደ በሚገኘው 38 የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ጸኃፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ÷ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አፍሪካ በቅኝ ግዛትና በባሪያ ንግድ ከፍተኛ በደል የደረሰበት አህጉር መሆኗን መዘንጋት እንደሌለበትና ተገቢውን ካሳ ማግኘት እንዳለባትም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ በመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ አለማግኘቷ ተገቢ አደለም፤ ስለሆነም አህጉሪቱ በምክር ቤቱ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እሰራለሁ ብለዋል።

ለአህጉሪቱ ሰላም እና ጸጥታ አበክሮ መስራት እንደሚገባም በመግለጽ በሱዳን እና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቆም አሳሳበዋል።

በማንኛውም ሁኔታ ቀጣናዊ ውጥረቶች መወገድ እንዳለባቸው ጠቅሰው÷የተባበሩት መንግስታትም ለአፍሪካ የሚደደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ሽብርተኝነት በአህጉሪቱ ላይ ያለው ተጽእኖ በቀላሉ መታየት እንዳሌለበትም ዋና ጸኃፊው አንስተዋል።

አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የምታደርገው አስተዋጾ አነስተኛ ቢሆንም በከፍተኛ ሁኔታ ተጎጂ በመሆኗ ፍትሃዊ የሆነ ካሳ እንደሚያስፈልጋት አመላክተዋል፡፡

ዋና ጸኃፊው አክለውም በእስራኤል እና በሀማስ መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚቀበሉት ገልጸው ስምምነቱ በቋሚነት እንዲጸና ጠይቀዋል።

በሔለን ታደሰ እና መሳፍንት ብርሌ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.