Fana: At a Speed of Life!

203 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 203 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ።

ወደ ሀገር ከተመለሱት 203 ዜጎች 151 ወንዶች፣ 36 ሴቶች እና 16 የሚሆኑት ደግሞ ጨቅላ ህፃናት መሆናቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለተመላሽ ዜጎች በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 90 ሺህ 916 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለሳቸው ታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.