Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን ኮሪያው መሪ ሶስት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በሀገራቸው እንዳይታዩ አገዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቶተንሃም ሆትስፐር፣ ዎልቭስ እና ብረንትፎርድ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን እንዳይታዩ ማገዳቸው ተገለፀ፡፡

ኪም ጆንግ ኡን ትዕዛዙን የሰጡት በሶስት ክለቦች የሚጫዎቱ የደቡብ ኮሪያ ተጫዋቾችን የሰሜን ኮሪያ ዜጎች እንዳይመለከቷቸው ለማድረግ ነው ተብላል፡፡

የቶተንሃም አምበል እና አጥቂ ሰን ሁንግ ሚን፣ የዎልቭሱ አማካይ ሀዋንገ ሂ ቻን እና የብረንትፎርዱ ተከላካይ ኪም ጂ ሶ የደቡብ ኮሪያ ዜግነት ያላቸው የፕሪሚየር ሊጉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

የማንቼስተር ዩናይትድ ደጋፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ኪም ጆንግ ኡን የስርጭት ክልከላውን ተከትሎ ዩናይትድ ዛሬ ምሽት ከቶተንሃም ሆትስፐር ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ አይመለከቱትም መባሉን ዘ ሰን ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.