ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ከ1 ነጥብ 16 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት በሰባት ወራት ውስጥ ከ233 ሺህ 340 ቶን በላይ የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ከ1 ቢሊየን 16 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።
ከቡና የወጪ ገበያ ብቻ በሰባት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊየን 11 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል።
ወደ ውጭ የተላከው የቡና ምርት ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን ከ96 ሺህ 780 ቶን በላይ በገቢ ደግሞ ከ383 ሺህ 47 ሚሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ እንዳለው ተገልጿል።
ሳዑዲ አረቢያ፣ ጀርመን እና ቤልጂየም ከኢትዮጵያ ቡና በመግዛት ቀዳሚዎቹ ሀገራት መሆናቸውም ተጠቁሟል።