Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በኦርሌን የ1 ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በኦርሌን የ1 ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር የራሷን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች

አትሌቷ ውድድሩን 3 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ ከ92 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ በራሷ ተይዞ የቆውን ክብረ ወሰን በ83 ማይክሮ ሰከንድ አሻሽላለች፡፡

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬን በመከተል አትሌት ብርቄ ሃየሎም እና ወርቅነሽ መሰለ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.