በአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጀመሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጀምረዋል።
በዚህ መሰረትም የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት አብዱልመጅድ ተቡን፣ የርዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ፣ የፍልስጤም መሪ መሐሙድ አባስ፣ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞተሊ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአዲስ አበባ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቅቀው ተመልሰዋል።
በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ የሴኔጋል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ፣ የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት አንድሬ ራጆሊና፣ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤምርሰን ምናንጋግዋ እና የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ሙባሎ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ለመሪዎቹ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር አሸኛኘት ያደረጉላቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።