8ኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 8ኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ፎረሙ “ከእመርታ ወደ ብልጽግና፤ የአፍሪካን ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች አቅም ማጠናከር” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች፣ የልማት ድርጅቶች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
የቢዝነስ ፎረሙ በአፍሪካ የቁም እንስሳት፣ግብርና ፣ ኢንዱስትሪና ሌሎች ዘርፎች እንዲሁም ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለት እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ልማት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡
በፎረሙ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት በዘርፎቹ ያሏቸው ተሞክሮዎቸ ፣ ቀጠይ ዕድሎች፣ ፈተናዎች እና መፍትሄዎች ቀርበው ምክክር እየተካሄደ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
በመራኦል ከድር