Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል እየተከናወኑ ባሉ መሠረተ ልማቶች ዙሪያ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በጋምቤላ ክልል እየተከናወኑ ባሉ መሠረተ ልማቶች ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋምቤላ ከተማ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ሚኒስቴሩ በ12 ክልሎችና በ27 ከተማ አስተዳደሮች በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የመደገፍና የመከታተል ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩ ድጋፍና ክትትል ከሚያደርግባቸው ክልሎች መካከል አንዱ የጋምቤላ ክልል መሆኑንም ነው የገለፁት።

ይህ ምክክርም ባለፉት ስድስት ወራት በመሠረተ ልማት ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎችን በመገምገም የቀጣይ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.